Upcoming Event:
  • 00

    days

  • 00

    hours

  • 00

    minutes

  • 00

    seconds

Upcoming Event:

  • 00

    days

  • 00

    hours

  • 00

    minutes

  • 00

    seconds

አደገችም ታላቅ ዛፍም ሆነች

Post

አደገችም ታላቅ ዛፍም ሆነች

…አደገችም ታላቅ ዛፍም ሆነች፥ የሰማይ ወፎችም በቅርንጫፎችዋ ሰፈሩ አለ…” ሉቃስ 13:19

በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ሳንሆዜ ሚሽን ቲም በትንሽ የተጀመረው የበጎ ስራ ዛሬ ለብዙ ልጆች፣ ወጣቶች እና ወላጆች መጠለያ ሆኖአል:: በእናንተ የቸርነት እና የፍቅር አገልግሎት ትምህርት ቤት መግባት ያልቻሉና በሜዳ ሊውሉ የነበሩወይም ያለ ዕድሜአቸው የጉልበት ስራ ሊሰሩ የነበሩ እንደ ሌሎች ልጆች በትምህርት ገበታ ላይ ሆነው መማር ጀምረዋል::

እንዲሁም አዳጊዎች እና ወጣቶች የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እና የኮሌጅ ትምህርታቸውን ያለምንም ስጋት መከታተል ችለዋል:: የተቀደደና ያረጀ ዩኒፎርም በመልበስ ያፍሩ የነበሩ ልጆች በየአመቱ አዲስ ዩኒፎርም በመልበስ ቀና ብለው ትምህርታቸውን ለመከታተል አቅም ሆኖላቸዋል:: እንዲሁም ደብተራቸውን በእጃቸው በመያዝ እየተቀደደ እና እየተበላሸ ይቸገሩ የነበሩ ልጆች በቦርሳ በመያዝ በነጻነት መውጣት እና መግባት ሆኖላቸዋል:: ባዶ እግራቸውን ወይም ያለቀ ጫማ በማድረግ ትምህርት ቤት እና ሌሎች ቦታዎች ሲሄዱ ይሸማቀቁ የነበሩ ልጆች ጫማ በማድረግ ያለፍርሀት መራመድ ጀምረዋል::

ስለልጆቻቸው በኑሮ ጫና ምክንያት ያለቅሱ የነበሩ ወላጆች በመጠኑም ቢሆን ችግራቸው ስለተላቀቀ በእናንተ እገዛ እንባቸው ታብሳóል:: ያዝኑ የነበሩ ወላጆች ተጽናንተዋል:: ልጆቻቻው ከሰው በታች እንደሆኑ ይሰማቸውና ይሸማቀቁ የነበሩ ወላጆች አሁን በሚደረግላቸው ድጋፍ ምክንያት ነፃነት ተሰምቶአቸዋል:: ትምህርት በየአመቱ ሊከፈት ሲል ስለልጆቻቸው ግራ ይገባቸው የነበሩ ምን እናደርጋለን? ምን እናለብሳቸዋለን? የትምህርት ቁሳቁስ እንዴት እናሟላላቸዋለን? የሚሉ ወላጆች በእናንተ በጎ ስራ እረፍት አግኝተዋል:: ልጆቻቸውን ለመመገብ እና አንዳንድ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ለማድረግ አቅም ያጡ ጥቂት ወላጆች ከእናንተ በሚያገኙት ወርሃዊ ድጋፍ ምክንያት ሸክማቸው በመጠኑ ተቃሎላቸዋል::

ቤተክርስቲያን ችግረኞችን ለመደገፍ የነበረባትን አቅም የማጣት ክፍተት በእናንተ በኩል ተሞልቶአል:: ሸክምንም አቃሎአል:: ከጭንቀቷም በከፊል አርፋለች:: በእናንተ ድጋፍ ምክንያት ቤተክርስቲያን ለችግረኞች ትጸልይ ለነበረው ጸሎት መልስ ሆናችዋል:: እግዚአብሔር በጥቂት የጀመራችሁትን ስራ ለብዙዎች መጠለያ፣ በረከት፣ መጽናናት፣ እረፍት፣ እፎይታ ሆኖአልና እግዚአብሔርን አመስግኑ::   

እግዚአብሔር እናንተን እና የእናንተ የሆነውን ሁሉ ይባርክ!! እግዚአብሔር አምላክ ጨምሮ ለብዙዎች እረፍት እና በረከት ያድርጋችሁ!!

ከኢትዮጵያ ቲም!!